የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር ባዘጋጁት በዚህ ውድድር ላይ ለተሳተፉ ተወዳዳሪዎች የእውቅና እና ሽልማት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።

በስነ ስርዓቱ በአጭር ጊዜ ተተግብረው መፍትሔ ሊያመጡ የሚችሉ 12 ፕሮጀክቶች ተለይተው እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የቴክኒክ ግምገማውን ያለፉ 30 ፕሮጀክቶች ደግሞ ወደ ቀጣዩ የግምገማ ሂደት አልፈዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ አቶ ግዛቸው ሲሳይ መሰል ችግር ፈች ፕሮጀክቶችን ለማገዝ ተቋሙ የበኩሉን ድርሽ እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.) በአጭር ጊዜ ውስጥ ወረርሽኙን ለመከላከል የቀረቡት የፈጠራ ሃሳቦች በሃገር ደረጃ እምቅ የፈጠራ ሃብት እንዳለ የተረዳንበት ነው ብለዋል፡፡

የተመረጡትን እነዚህን ፕሮጀክቶች ወደመሬት በማውረድ ህበረተሰቡ እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ የተሟላ ድጋፍ እንደሚደረግ እና ሌሎች በግሉ ዘርፍ ያሉ ተቋማትም ፈጠራዎቹ ወደ ንግድና ሐብት ፈጠራ እንዲቀይሩዋቸው ሚኒስትር መስሪያቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡

Source: (http://mint.gov.et/-/-19-446-12-?inheritRedirect=true&redirect=%2F-%2F-3-)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here